+251924381169  info@haqi.org
Follow us

እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት

  • በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ክልሉ ሊታሰብ ለማይችሉ ችግሮች ተዳርጓል።

  • በአስከፊው ጦርነት ምክንያት እንደማንኛው ማህበረስብ የተደጎዱ ቢሆኑም የጤና እንክብካቤና መምህራን ሌሎች በጦርነቱ የተጎዱትን የህብረተሰብ ክፍሎችን መንከባከብ ይጠበቅባቸዋል።

  • ራሳቸው የጦርነት ሰለባ ሆነው ለህብረተሰቡ የጤና እንክብካቤ እና ትምህርት እንዲሰጡ የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ምክንያት ከእነሱ የሚጠበቀውን አገልግሎት በብቃት የማቅረብ አቅማቸውን አደጋ ላይ ወድቋል። . 

  • እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት በሺዎች ለሚቆጠሩ የጤና እንክብካቤ እና የትምህርት ባለሙያዎች አስፈላጊ ድጋፍ በማድረግ ለታካሚዎቻቸው እና ለተማሪዎቻቸው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንክብካቤን እንዲሰጡ ለማስቻል የሚሰራ ፕሮጀክት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ


ሰጋር ስኮላርሺፕ የምክር እና የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት  

  • በትግራይ ክልል   የተካሄደው ጦርነት በክልሉ የትምህርት ስርዓት ላይ በማያሻማ መልኩ እንዲሁም  በክልሉ የሰው ሃይል ካፒታል ላይ ትልቅ ተፅኖ  ፈጥርዋል። በትምህርት ቤቶችና በመምህራን ላይ በደረሰው ውድመት ጋር ተያይዞ ሕፃናትና ወጣቶች የትምህርት ዕድል እንዳይኖራቸው አድርጓል፡፡

  • በትግራይ ውስጥ በመጀመሪያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቀጥሎም በአሰቃቂው ጦርነት ምክንያት የትግራይ ህፃናት እና ወጣቶች ከሦስት ዓመታት በላይ  የትምህርት ዓመታትን ያለትምህርት አሳልፈዋል።

  • በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስራ ፈላጊ ወጣቶች በልህቀትና እና በስራ ፈጠራ ለመሰማራት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲቀላቀሉ በሚያደርጋቸው የትኩረት የስልጠና እድሎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት እድልን ማመቻቸት ወደ ኋላ የማይባል ነው።

    ትግራይን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት  የሚያስፈልጉ እውቀቶችንና ክህሎቶችን ለማመንጨት የሚያግዝ የትምህርት እድሎችን መስጠት እንዲሁም የአጭር ጊዜ የታለመ ስልጠና ማዘጋጀት ቁልፍ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ


መልሶ የመገንባት መንገድ

  • ጦርነቱ ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የትግራይ  መሠረተ ልማቶች ከማውደም ባለፈ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን አውድሟል።

  • ይሁን እንጂ የጥፋቱ መጠንና ክብደት ምንም የከፋ ቢሆንም እንኳ ከሌሎች አገሮች ታሪክ መረዳት እንድሚቻልው በትክክለኛ ፖሊሲዎች እና ትክክለኛ የፖለቲካ እና ተቋማዊ አደረጃጀት በፍጥነት ማገገም የሚቻልበት መንገድ አለ፡፡

  • ትግራይ በታሪካቸው ከጦርነት አገግመው የተሳካ የማህበረሰባዊና የኢኮኖሚ ለውጥ ካመጡ ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ የክልሉን ኢኮኖሚ  በዘላቂነት ለማልማት አዳዲስ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ማዘጋጀት ይቻላል።

ተጨማሪ ያንብቡ

" የማገገሚያ ሂደቱን ለመደገፍ ያለመ የፕሮጀክት እና  ሃሳብ ካሎት እባክዎ ያነጋግሩን እና አብረን እንስራ"