ስለ HAQI ፋውንዴሽን
አንድን ኢኮኖሚ መልሶ ለመገንባት የላቁ ሀሳቦችን እንደሚፈልግ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ከመጠነ ሰፊ ውድመት ለማገገም ሁሉን አቀፍ እና የሁሉን መጠነ ሰፊ ተሳትፎ ይጠይቃል። ሓቂ ፋውንዴሽን በማስረጃ የተደገፉ ሀሳቦች ላይ በመስራት ትግራይን ወደ ነበረበት ለመመለስ እና በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ታቅዶ የተዘጋጀ መድረክ ነው።
ሓቂ, የጥሬ ቃል ትርግሜው እውነት ማለት ሲሆን መጀመሪያ ቃሉ መጠሪያ እነዲሆን ከተወሰነ በኋላ ለ HAQI ለእያንዳንዱ ፊደል አንድ ቃል በመስጠት ምህጻረ ቃሉ ሰብአዊነትን፣ ብልህነትን፣ ጥራትንና ቀናነትን ይይዛል።ተቆርቋሪንት በሚሰማችዉ ግለሰቦች የተቋቋመው ሓቂ ፋውንዴሽን ትግራይን መልሶ ለመገንባት ስልቶችን፣ ማዕቀፎችን እና የተሳትፎ መድረኮችን በማዘጋጀት እና አንድ ላይ በመስራት የተሻለ ዉጤቱ ማግኘት እንደሚቻል ያምናል። ሁሉም በጎ አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች ለትግራይ ያላቸውን ሃሳብ፣ ምኞቶች እና ህልሞች በማካፈል ለትግራይ ተሃድሶ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ናቸው። መልሶ መገንባት የሚጀምረው ግልጽ፣ አስፍላጊነት ባላቸው እና ማህበረሰቡን በአማከሉ ሃሳቦች ነው።
ሓቂ ሰረት ብጥበብ ኢሂን ሚሂን ተባሃሂልና ብንምህዞም ሜላታትን ስራሕትን ዳግመ ህንፀትን ሕውየትን ትግራይ ንምርጋግፅ ግዱሳት ተጋሩ ዝፈጠርዎ መድረኽ እዩ ። ዓበይቲ ሓሳባት ዝ ህቀኑሉን ዝትግበሩሉን ሰረት ንክኸውን ኩሎም ሓሳብ ዘለዎም ተጋሩን ፈተውቲ ትግራይን ምሳና ክሰርሑ ንዕድም።
ሓቂ ፋውንዴሽን ተመካክረን ሃሳቦችን አሰላስለን በማቀድና በመተግበር የትግራይን ዳግም ግንባታ እና እድገትን ለማረጋገጥ ተቆርቋሪ ዜጎች የፈጠሩት መድረክ ነው ። ትግራይን መልሶ ለመገንባት የሚጠቅሙ ሃሳቦችዎን እያጋሩን አብረውን ይሰሩ ዘንድ ተጋብዘዋል።

ተደራሽነታችን
ዓመታት
አጋዦች
ፕሮጀክቶች
Mental Health Training
The Tigray war has left deep scars on
the hearts and minds of countless people. The trauma and emotional distress
resulting from the conflict demand urgent attention. Recognizing the critical
importance of addressing mental health in post-war recovery, HAQI Foundation
has taken the initiative to establish a specialized program to address these
pressing needs.
Trainings provided by HAQI's mental health experts
1. Daughters of charity's Volunteers (10 in number) 5 days training on PFA and Psychosocial support
2. Ministry of Revenue (360 trainees) 2 days on 2 session Psychological healing and Trauma Informed care
3. Customs around 216 in number. 2 days on 2 sessions.
ስራዎቻችን
ሓቂ ብዙ ፕሮጀክቶች እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩት እንገምታለን፡፡ ነገርግን HAQI ለመነሻነት ትኩረትሰጥቶ የሚንቀሳቀስባቸው ዋና ዋና ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው።

1. እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት
( እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት)
“To care for those who care for others is one of the highest honors!” —Tia Walker, author
እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት - በጦርነቱ ምክንያት በጤና እንክብካቤ እና በትምህርት ባለሙያዎች የአእምሮ እና የአካል ጉዳትን ጨምሮ የአገልግሎት መስተጓጎሉ እንክብካቤ በሚሰጡ ባለሞያዎቹ ላይ ምን ያህል ተጸእኖ እና ክብደትን እንዳደረሰ ለመለየት ያለመ ጥናት ነው፡፡ በጥናቱ ዉጤት መሰረትም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመንደፍ እና የማገገሚያ ሂደቱን በማገዝ፤ የራሳቸውን ደህንነት እንዲሁም የሕመምተኞችን፣ የተማሪዎችን እና የሌሎች በጦርነቱ የተጎዱ ሰዎችን የማገዝ አቅማቸው እንዲጠናከር የሚሰሩ ፕሮግራሞችን ለመንደፍ የሚሰራ ፕሮጀክት ነው።

2. መልሶ የመገንባት መንገድ
(መልሶ የመገንባት መንገድ)
“Only a fool learns from his own mistakes. The wise man learns from others.” — Otto von Bismarck
ለፖሊሲ ውይይቶችና የትግራይን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም መለሶ በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ጠንካራ መሰረት ያለው ከሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታ በአስከፊ ጦርነት ዉስጥ አልፈው የተሳካ የኢኮኖሚ ማገገሚያ ካደረጉ አገሮች ሊዳብር ይችላል። ይህ ፕሮጀክት የሚያተኩረው ከሌሎት ልምምዶች፣ ትምህርቶች እና ቤንችማርኪንግ ላይ በመነሳት መልሶ ኢኮኖሚን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት የሚያገለግሉ ስልቶችን እና ፕሮግራሞችን በመለየት ላይ ነው።

3. ሰጋር የትምህርት ዕድል
(ሰጋር ስኮላርሺፕ)
“Give a man a fish, and he will eat for a day. Teach a man to fish, and he will eat for a lifetime.” —Laozi
የዚህ ፕሮጀክት አላማ የትግራይ ወጣቶች የአጭር ጊዜ እና የረዥም ጊዜ የስኮላርሺፕ ዕድሎችን እና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የምክር እና የመረጃ አገልግሎት በመስጠት የክልሉን የሰው ሀይል አቅም ማሳደግ ነው፡፡ አዳዲስ ዜናዎች እና ማስታወቅያዎች

ተጨማሪ ያንብቡ


ምኞቴ ለትግራይ
(ትምኒተይ ንትግራይ)
“ Tell me what your vision of the future and I will tell you what you are. ” — Fred Polak
በየትኛውም የዓለም ክፍል ያያችኋቸው ወይም ያጋጠማቹህ ነገሮች በትግራይ እንዲፈጸሙ የምትመኙት ነገር ይኖር ይሆን? “ ይህ
በፍፁም በትግራይ መከሰት የለበትም!” ያላችኋቸው የታዘባችኋቸው ሁኔታዎች አሉ? ለትግራይ ምን ትመኛለህ/ሽ? ማህበራዊ
እና ኢኮኖሚያዊ እድገት? ጥራት ያለው ትምህርት እና የጤና አገልግሎት ለሁሉም ነዋሪ? የአንድነት ስሜት ያለው ጠንካራ እና
ንቁ ማህበረሰብ? በእግረኛ መንገድ በፀሃይ ፓነሎች የተከለሉ መንገዶች? በ 10 እጥፍ የበለጠ ውጤታማ የግብርና ልምዶች?
ለሁሉም ማህበረሰብ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና መሰረታዊ ፍላጎቶች መሟላት፣ወጣቶች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ዕድሎች ማመቻቸት
፣ሰላም እና መረጋጋት?
የትግራይ ልጆች
(ቆልዑ
ትግራይ)
“We owe it to our children to give them a dignified and hopeful future.” —Giorgio Napolitano
የትግራይ ልጆች ጥራት ያለው ሕይወት የሚመሩበት፣ ጥራት ያለው ትምህርት የሚያገኙበት፣ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት፣ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት አስተማማኝና የተረጋጋ አካባቢ ይገባቸዋል። ለእነዚህ ልጆች የተሻለ ዓለም ለመፍጠር አብረን እንስራ፡፡
ለልጆቻችን የተሻለ ዓለም ለመፍጠር ሀሳቦችዎን ያካፍሉን፡፡

ደስተኛ አስተማሪዎች
(ታሕጓስ)
“A teacher affects eternity; he can never tell where his influence stops.” —Henry Adams
በትግራይ ጦርነት መክንያት የተጎዱ መምህራንን ደህንነት ለማስጠበቅና ለማሳደግ ያለመ ፕሮግራም ነው። አላማችን አስተማሪዎች በግል እና በሙያዊ ህይወታቸው ውስጥ ከፍተኛ ተነሳሽነት፤ አክብሮትን እና ደስታን እንዲያገኙ በመስራት የተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት መፍጠር ነው። መምህራን ደስተኛ እንዲሆኑ ለመደገፍ እና ለመርዳት እንጥራለን፡፡
በትግራይ ደስተኛ መምህራንን ለመፍጠር ሀሳብዎን ያካፍሉ!