+251924381169  info@haqi.org
Follow us

ሓቂ ነፃ የስልክ መስመር

 

ሓቂ ነፃ የእርዳታ የስልክ መስመር ምንድን ነው?

እንኳን ወደ ሓቂ ነፃ የእርዳታ የመስመር ስልክ በደህና መጡ! ሓቂ ነፃ የእርዳታ የመስመር ስልክ ሰኔ 19፣ 2023 በሓቂ ፋውንዴሽን ስር የተመሰረተው ወሳኝ የአእምሮ ጤና አገልግሎት የሚሰጥበት የመስመር ስልክ ነው። ይህ የስልክ መስመር በአእምሮ ጤና ዙርያ ድጋፍ እና መመሪያ ለሚሹ ወገኖች ነፃ፣ ሚስጥራዊነቱ የጠበቀ፣ ሩህሩህና ከአድልዎ የፀዳ አገልግሎት የሚሰጥበት መድረክ ነው። ይህ አገልግሎት ለመጠቀም ከሚገኙበት የትግራይ አከባቢ ወደ 8516 ይደውሉ። ሓቂ ነፃ የእርዳታ የመስመር ስልክ በጦርነት በተጎዳው በትግራይ ክልል በተለያየ የህብረተሰቡ አካላት ላይ ያጋጠመው ሰፊ የስነ አእምሮአዊና ስነልቦናዊ ችግሮች ለመፍታት፣ የአእምሮ ደህንነትን ለማሳደግ እና ለማበረታታት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። 

እንደ ሓቂ ፋውንዴሽን፤ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ ማህበረሰብ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ኣካላዊ እንዲሁም ለከፍተኛ የአእምሮ ጤና ችግሮችና ልዩ ፈተናዎች እንደተጋለጠ ይረዳል። ድርጅታችን ይህን ፕሮጀክት የጀመረው በክልሉ ያልውን የችግሩን ክብደት በመገንዘብ በአእምሮ ጤና ዙርያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በመድረስ ችግሩን ለማቃለልና የበኩሉን ድርሻ ለመውጣት ነው። ድርጅታችን ማንኛውም የአእምሮ ጤንነት ችግር ያጋጠመው ሰው ያለፍርድ እና ያለመገለል ድምፁ ሊሰማ እንዲሁም ጭንቀቱ ሊፈታለት ይገባዋል ብሎ በፅኑ ያምናል።ዓላማችን

የሓቂ ነፃ የእርዳታ የስልክ መስመር ለደዋዮች ሰሚ ጆሮን ከመስጠት ያለፈ ነው። በምንሰጠው አገልግሎት በማህበረሰቡ ላይ በሚያጋጥመው የሰነ አእምሮ ጤንነት ችግር መሻሻል ለማምጣት በቁርጠኝነት እንተጋለን።

የትምህርት ተነሳሽነት

ደዋዮቻችንን ስለተለያዩ የአእምሮ ጤና መታወክ፣ የሕክምና አማራጮች፣ የመቋቋሚያ ዘዴዎች እንዲሁም እርዳታ የመሻትና የመጠየቅ አስፈላጊነት ለማስተማር ዓላማ እናደርጋለን። ትክክለኛ እና አስተማማኝ መረጃ በማቅረብ ግለሰቦች ስለአእምሮ ጤና አጠባበቅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ እናበረታታለን። 


መገለልን ማጥፋት

የአእምሮ ጤንነት ችግር በህብረተሰባችን ውስጥ ኣሁንም የአድልዎና የመገለል ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል። በቅን እና ግልፅ በሆኑ ውይይቶች እንዲሁም በተለያዩ አስተማሪ የሆኑ የግል ታሪኮችን በማካፈል፤ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማስቀረት በአእምሮ ጤና ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን የህብረተሰቡ የማግለል እና የመፀየፍ ባህርይ ለመቀነስ ተግተን እንሰራለን። ግባችን በእውቀት የተመሰረተ መረዳዳት በማጎልበት ይበልጥ ተግባቢ እና ተደጋጋፊ ማህበረሰብ መፍጠር ነው።  


ለደዋዮች ምቹ፣ ቀላልና አሳታፊ መድረክ መፍጠር 

ደዋዮቻችን በእገዛ መስመራችን እየደወሉ በንቃት እንዲሳተፉ እናበረታታለን። ደዋዮች ወደ እገዛ መስመራችን በነፃነት የመደወል፣ ልምዶቻቸውን በግልፅነት የማካፈል፣ ጥያቄዎችን ያለምንም ስጋት የመጠየቅ እንዲሁም በውይይት መድረኮች የመሳተፍ ልምዶቻቸውን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን። የማህበረሰባዊነት ስሜት በመፍጠርና በማሳደግ ስለ የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች ክፍት ውይይት እንዲደረጉ እናበረታታለን። በተጨማሪም ግለሰቦች እርስ በርስ የሚገናኙበት እና የሚደጋገፉበት አስተማማኝ ቦታ እንዲመቻችላቸው እንጥራለን። 

ከባለሙያዎቻችን ለደዋዮች ሞያዊ ግንዛቤ ማጋራት

ባለሙያዎቻችን በዘርፉ የተማሩ፣ በተለያዩ ስልጠናዎች የበቁ፣ የማማከር ልምድ እና የህይወት ተሞክሮ ባላቸውን ግለሰቦች የያዘ ነው። የባለሙያዎቻችን ግንዛቤ የአእምሮ ጤና ስጋቶችን ለመፍታት ተግባራዊ መፍትሄዎችን ለደዋዮቻች ይሰጣል። ይህም ታማኝ መረጃዎች፣ ምክሮችና ግብአቶችን ያካትታል።

በደዋዮች እርዳታ የመሻትና የመጠየቅ ልምድን ማሳደግ

በስኬት ታሪኮች እና በሚገኙ ግብአቶች አማካኝነት ግለሰዎች በስነ ኣእምሮኣዊ ጉዳዮች ላይ እርዳታ የመሻትና በግልፅ የመጠየቅ ባህሪን ለማሳደግ ዓላማ አለን። የውይይት መድርኮቻችን ስለ ነፃ የእርዳታ መስመራችን ኣጠቃቀም እንዲሁም ስለ የምንሰጣቸው የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች መረጃ ያገኙበታል፤ ይህም ደዋዮች ያለ ማመንታት ድጋፍ እንዲጠይቁና ድጋፍ እንዲያገኙ ያበረታታል። 

ባለሞያዎቻችን እንደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ የስነ አእምሮ ቁስሎች እና ከውጥረት ጋር የተገናኙ ህመሞችን ጨምሮ የተለያዩ የአእምሮ ጤና ጉዳዮችን ለመፍታት የሚያስችል እውቀት እና ልምድ የያዙ ናቸው። የአእምሮ የጤንነት ጉዞዎን በድል ለመምራት እንዲረዳዎ ተገልጋዩ መሰረት ያደረገና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ።

ወደ ሓቂ የእርዳታ የስልክ መስመር ሲደውሉ፣ ከባለሙያዎቻችን ከፍርድ እና ከአድልዎ ነፃ የሆን እንዲሁም ርህራሄ የተሞላበት አገልግሎት ያገኛሉ። ባለሙያዎቻችን የደዋዮችን ስጋቶች በንቃትና በጥሞና ያደምጣሉ፣ ለደዋዮች ሞያዊ መመሪያ ይሰጣሉ። በተጨማሪም ደዋዮቹን መሰረት ያደረጉ ኣስፈላጊ ልዩ የመቋቋሚያ ስልቶችን እና ግብዓቶችን ይሰጣሉ። በነፃ የእርዳታ የስልክ መስመራችን የሚደረጉ ማናቸውም የስልክ ንግግሮች የደዋዮቻችን ግላዊነት እና ደህንነት በሚያረጋግጥ ጥብቅ እና ሚስጥራዊ መሆናቸውን እርግጠኞች ይሁኑ።

የአእምሮ ጤና እርዳታ ለሁሉም ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ ተሞክሮ ያካተተ መሆን አለበት ብለን እናምናለን። በአእምሮ ጤናዎ ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ልዩ ባህላዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ባለሙያዎቻችን በቅንነትና በህላፊነት ድጋፍ ለመስጠት የሰለጠኑ ናቸው። 

በሓቂ ነፃ የእርዳታ የስልክ መስመር አማካኝነት በትግራይ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በአእምሯዊ ደህንነት ላይ በጎ ተፅእኖ ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን። ባለሙያዎቻችን ተገልጋዮች የአእምሮ ጤንነታቸው መልሰው እንዲቆጣጠሩ እና አርኪ ህይወት እንዲኖራቸው ለመርዳት የተጉ ናቸው። ተገልጋዮቻችን ለማበረታታት፣ ሰሚ ጆሮ ለመስጠት እና የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ እና ግብዓቶች ለማድረግ እንተጋለን። 

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው ከአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች ጋር እየታገለ ከሆነ፤ ወደ ሓቂ ነፃ የእርዳታ መስመር በ8516 ኣሁኑኑ ለመደወል አያመንቱ። ባለሙያዎቻችን እርስዎን ለማዳመጥ፣ ለመደገፍ፣ ወደ ፈውስና ደህንነት ለመምራት ተግተው ይሰራሉ።

ያስታውሱ፤ ብቻዎትን አይደሉም! የሚፈልጉትን ድጋፍ እና እርዳታ ለመስጠት የሓቂ ነፃ የእርዳታ የስልክ መስመር እዚህ አለ። አሁንኑ ወደ ነፃ የእርዳታ የስልክ መስመራችን በ8516 ይደውሉና ወደ ጤናማና ደስተኛ ህይወት የሚወሰደው የመጀመሪያውን እርምጃዎን መራመድ ይጀምሩ።