+251924381169  info@haqi.org
Follow us

እንኳን ወደ HAQI በደህና መጡ !

እውነት እና ተስፋ የሚያበሩበት፡ መስጠት ዘላለማዊ የሚሆንበት !


​ 

                                                                                                                                                                                                                                                     


ስለ HAQI ፋውንዴሽን

አንድን ኢኮኖሚ መልሶ ለመገንባት የላቁ ሀሳቦችን እንደሚፈልግ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ከመጠነ ሰፊ ውድመት ለማገገም ሁሉን አቀፍ እና የሁሉን መጠነ ሰፊ ተሳትፎ ይጠይቃል። ሓቂ ፋውንዴሽን በማስረጃ የተደገፉ ሀሳቦች ላይ በመስራት ትግራይን ወደ ነበረበት  መመለስ እና በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ታቅዶ  የተዘጋጀ መድረክ ነው።

ሓቂ, የጥሬ ቃል ትርግሜው እውነት ማለት ሲሆን መጀመሪያ ቃሉ መጠሪያ እነዲሆን ከተወሰነ በኋላ ለ HAQI ለእያንዳንዱ ፊደል አንድ ቃል በመስጠት ምህጻረ ቃሉ ሰብአዊነትን፣ ብልህነትን፣ ጥራትንና ቀናነትን ይይዛል።

ተቆርቋሪንት በሚሰማችዉ ግለሰቦች የተቋቋመው ሓቂ ፋውንዴሽን ትግራይን መልሶ ለመገንባት ስልቶችን፣ ማዕቀፎችን እና የተሳትፎ መድረኮችን በማዘጋጀት እና አንድ ላይ በመስራት የተሻለ ዉጤቱ ማግኘት እንደሚቻል ያምናል። ሁሉም በጎ አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች ለትግራይ ያላቸውን ሃሳብ፣ ምኞቶች እና ህልሞች በማካፈል ለትግራይ ተሃድሶ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ናቸው። መልሶ መገንባት የሚጀምረው ግልጽ፣ አስፍላጊነት ባላቸው እና ማህበረሰቡን በአማከሉ ሃሳቦች ነው።

ሓቂ ሰረት   ብጥበብ ኢሂን ሚሂን ተባሃሂልና ብንምህዞም ሜላታትን ስራሕትን ዳግመ ህንፀትን ሕውየትን ትግራይ ንምርጋግፅ ግዱሳት ተጋሩ ዝፈጠርዎ መድረኽ እዩ ። ዓበይቲ ሓሳባት ዝ ህቀኑሉን ዝትግበሩሉን ሰረት ንክኸውን ኩሎም ሓሳብ ዘለዎም ተጋሩን ፈተውቲ ትግራይን ምሳና ክሰርሑ ንዕድም።  

ሓቂ ፋውንዴሽን  ተመካክረን ሃሳቦችን አሰላስለን በማቀድና በመተግበር የትግራይን ዳግም ግንባታ እና እድገትን ለማረጋገጥ ተቆርቋሪ ዜጎች የፈጠሩት መድረክ ነው ። ትግራይን መልሶ ለመገንባት የሚጠቅሙ ሃሳቦችዎን እያጋሩን አብረውን ይሰሩ ዘንድ ተጋብዘዋል።

 

ተደራሽነታችን

2
ዓመታት 
3+ 
አጋዦች 
3 
ፕሮጀክቶች
 

Mental Health Training

The Tigray war has left deep scars on the hearts and minds of countless people. The trauma and emotional distress resulting from the conflict demand urgent attention. Recognizing the critical importance of addressing mental health in post-war recovery, HAQI Foundation has taken the initiative to establish a specialized program to address these pressing needs. 
Trainings provided by HAQI's mental health experts

1. Daughters of charity's Volunteers (10 in number) 5 days training on PFA and Psychosocial  support
2. Ministry of Revenue (360 trainees) 2 days on 2 session Psychological healing and Trauma  Informed care
3. Customs  around 216 in number. 2 days on 2 sessions.




ስራዎቻችን

ቂ ብዙ ፕሮጀክቶች እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚኖሩት እንገምታለ፡፡ ነገርግን HAQI ለመነሻነት ትኩረትሰጥቶ የሚንቀሳቀስባቸው ዋና ዋና ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው።

Your Dynamic Snippet will be displayed here... This message is displayed because you did not provided both a filter and a template to use.

1. እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች  ፕሮጀክት 

( እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት)

“To care for those who care for others is one of the highest honors!” —Tia Walker, author

እንክብካቤ ለእንክብካቤ ሰጪዎች ፕሮጀክት - በጦርነቱ ምክንያት በጤና እንክብካቤ እና በትምህርት ባለሙያዎች የአእምሮ እና የአካል ጉዳትን ጨምሮ የአገልግሎት መስተጓጎሉ እንክብካቤ በሚሰጡ ባለሞያዎቹ ላይ ምን ያህል ተጸእኖ እና ክብደትን እንዳደረሰ ለመለየት ያለመ ጥናት ነው፡፡ በጥናቱ ዉጤት መሰረትም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመንደፍ እና የማገገሚያ ሂደቱን በማገዝ፤ የራሳቸውን ደህንነት እንዲሁም የሕመምተኞችን፣ የተማሪዎችን እና የሌሎች በጦርነቱ የተጎዱ ሰዎችን የማገዝ አቅማቸው እንዲጠናከር የሚሰሩ ፕሮግራሞችን ለመንደፍ የሚሰራ ፕሮጀክት ነው

2. መልሶ የመገንባት መንገድ 

(መልሶ የመገንባት መንገድ)

“Only a fool learns from his own mistakes. The wise man learns from others.” — Otto von Bismarck

ለፖሊሲ ውይይቶችና የትግራይን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም መለሶ በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ጠንካራ መሰረት ያለው ከሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታ በአስከፊ ጦርነት ዉስጥ አልፈው የተሳካ የኢኮኖሚ ማገገሚያ ካደረጉ አገሮች ሊዳብር ይችላል። ይህ ፕሮጀክት የሚያተኩረው ከሌሎት ልምምዶች፣ ትምህርቶች እና ቤንችማርኪንግ ላይ በመነሳት መልሶ ኢኮኖሚን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባት የሚያገለግሉ ስልቶችን እና ፕሮግራሞችን በመለየት ላይ ነው።

3. ሰጋር የትምህርት ዕድል    

 (ሰጋር ስኮላርሺፕ)       

“Give a man a fish, and he will eat for a day. Teach a man to fish, and he will eat for a lifetime.” —Laozi

የዚህ ፕሮጀክት አላማ የትግራይ ወጣቶች የአጭር ጊዜ እና የረዥም ጊዜ የስኮላርሺፕ ዕድሎችን እና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ  የምክር እና የመረጃ አገልግሎት በመስጠት የክልሉን የሰው ሀይል አቅም ማሳደግ  ነው፡፡     
 

 አዳዲስ ዜናዎች እና ማስታወቅያዎች 

Mental Health and Psycho-social Support (MHPSS) Training for Ethiopian Red Cross Society Staff and Volunteers
ተጨማሪ ያንብቡ
Mental Health Training for Bureau of Lands and Minerals Staff in Tigray Post-Crisis
ተጨማሪ ያንብቡ
HAQI Foundation Launches Toll-Free Helpline for Psychosocial Support in Tigray
ተጨማሪ ያንብቡ
                                                                                    ተጨማሪ ዜናዎችና እና ማስታወቅያዎች ይመልከቱ


ምኞቴ ለትግራይ  

(ትምኒተይ ንትግራይ)  

Tell me what your vision of the future and I will tell you what you are. ” — Fred Polak

በየትኛውም የዓለም ክፍል ያያችኋቸው ወይም ያጋጠማቹህ ነገሮች በትግራይ እንዲፈጸሙ የምትመኙት ነገር ይኖር ይሆን? “ ይህ  በፍፁም በትግራይ መከሰት የለበትም!” ያላችኋቸው የታዘባችኋቸው ሁኔታዎች አሉ? ለትግራይ ምን ትመኛለህ/ሽ? ማህበራዊ  እና ኢኮኖሚያዊ እድገት? ጥራት ያለው ትምህርት እና የጤና አገልግሎት ለሁሉም ነዋሪ?  የአንድነት ስሜት ያለው ጠንካራ እና  ንቁ ማህበረሰብ? በእግረኛ መንገድ በፀሃይ ፓነሎች የተከለሉ መንገዶች? በ 10 እጥፍ የበለጠ ውጤታማ የግብርና ልምዶች?  ለሁሉም ማህበረሰብ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና መሰረታዊ ፍላጎቶች መሟላት፣ወጣቶች ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ዕድሎች ማመቻቸት  ፣ሰላም እና መረጋጋት? 

ይህን ትግራይ ውስጥ ማየት እመኛለሁ የሚሉትን፤ ያዩትን ወይም ያሰቡትን ይንገሩን እና ከእኛ ጋር በአጋራነት አብረን በመስራት በትግራይ እውን የሚሆንበትን መንገድ እንፈልግ!

የትግራይ ልጆች  

(ቆልዑ ትግራይ)

“We owe it to our children to give them a dignified and hopeful future.” —Giorgio Napolitano

የትግራይ ልጆች ጥራት ያለው ሕይወት የሚመሩበት፣ ጥራት ያለው ትምህርት የሚያገኙበት፣ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት፣ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት አስተማማኝና የተረጋጋ አካባቢ ይገባቸዋል። ለእነዚህ ልጆች የተሻለ ዓለም ለመፍጠር አብረን እንስራ፡፡ 

 
ለልጆቻችን የተሻለ ዓለም ለመፍጠር ሀሳቦችዎን ያካፍሉን፡፡

ደስተኛ አስተማሪዎች

(ታሕጓስ)   

“A teacher affects eternity; he can never tell where his influence stops.” —Henry Adams

በትግራይ ጦርነት መክንያት የተጎዱ መምህራንን ደህንነት ለማስጠበቅና ለማሳደግ ያለመ ፕሮግራም ነው። አላማችን አስተማሪዎች በግል እና በሙያዊ ህይወታቸው ውስጥ ከፍተኛ ተነሳሽነት፤  አክብሮትን እና ደስታን እንዲያገኙ በመስራት የተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት መፍጠር ነው። መምህራን ደስተኛ እንዲሆኑ ለመደገፍ እና ለመርዳት እንጥራለን፡፡ 

በትግራይ ደስተኛ መምህራንን ለመፍጠር ሀሳብዎን ያካፍሉ!